SportSports

ሊቨርፑል እና ቶተንሃም የቻምፒዮንስ ሊግ ጉዟቸውን በድል አስቀጥለዋል

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት መካሄድ ጀምረዋል፡፡

የእንግሊዙ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ የፖርቱጋሉን ፖርቶ አስተናግዶ 2 ለ 0 ድል በማድረግ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ለማለፍ መልካም ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ለቀያዮቹ የአሸናፊነት ጎሎችን ጊኒያዊ አማካይ ናቢ ኬይታ እና ብራዚላዊው ሮቤርቶ ፊርሚኖ በመጀመሪያው የጨዋታው አጋማሽ ውስጥ ማስቆጠር ችለዋል፡፡

እንግዳው ቡድን በአጥቂው ሙሳ ማሬጋ አማካኝነት የግብ እድሎችን ቢፈጥርም ወደ ግብነት መቀየር ሳይችል ቀርቷል፡፡

በሌላኛው ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐር በሜዳው ማንችስተር ሲቲን 1 ለ 0 በመርታት በአዲሱ ስታዲየም ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ፤ በምሽቱ ያሳካው ድል ለመልሱ ግጥሚያ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሮለታል፡፡

ደቡብ ኮሪያዊው ሰን ሁንግ ሚን መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ 12 ደቂቃዎች ሲቀሩ የቡድኑን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል፡፡

የጓርዲዮላው ሲቲ በመጀመሪያው የጨዋታው ክፍለ ጊዜ፤ ስተርሊንግ የመታውን ኳስ ዳኒ ሮዝ በእጁ ነክቷል በሚል የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት አጥቂው ሰርጂዮ አጉዌሮ መትቶ ሁጎ ሎሪስ ግብ እንዳትሆን አምክኗል፡፡

የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች የሚቀጥለው ሳምንት ዕረቡ ይከናወናሉ፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami