የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከግንቦት 21 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112 በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ የካቲት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ታትሞ ወጥቶ ነበር
በአዋጁ አንቀጽ 74(4) መሰረት የአልኮል መጠጥ በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) አማካኝነት ማስተዋወቅ የሚከለክለው ድንጋጌ ከግንቦት 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
በዚሁ መሰረት ማንኛውም የአልኮል መጠጥ የማስታወቂያ አስነጋሪ እና የብሮድካስት ሚድያ ለህጉ ተፈጻሚነት ተገቢውን ዝግጅት እንድያደርጉ እና ለህጉ መፈጸም የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጤና ሚኒስቴር ጠይቋል፡፡