Uncategorized

ስድስት የዕሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን ከደቡብ አፍሪካ ሊመጡ ነው።

ስድስት የዕሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን ከደቡብ አፍሪካ ሊመጡ ነው።
 
የኬንያ መንግስት የተጠየቀውን የእሳት አደጋ መቆጣጠሪያ አውሮፕላኖች ድጋፍ ማድረግ ያልቻለው በኬኒያ ፓርኮች ላይ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በመነሳቱ መሆኑን አስታውቃል።
 
በሰሜን ተራሮች ላይ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ሳቢያ የኢትዮጵያ መንግስት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የደቡብ አፍሪካ መንግስት 6 የዕሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን ለመላክ መስማማቱ ተነግሯል።
 
በተመሳሳይም የፈረንሳይ መንግስት ለዚሁ የድጋፍ ጥሪ ምላሽ ተግባራዊ ለመስጠት ፍቃደኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን እስካሁን ድረስ የድጋፉ አይነት ምን አንደሆነ አልታወቀም።
 
መንግስት ይህንን ሰደድ እሳት መቆጣጠር ከአቅሙ በላይ መሆኑን በማስታወቅ የኬንያ መንግስትን የእሳት መከላከያ አውሮፕላኖች ጠየቆ አንደነበር ይታወሳል።
 
የኬኒያ መንግስት አውሮፕላኖቹን ለመስጠት ተስማምቶ የነበረ ሲሆን በኬንያ ፓርኮች ላይ ቃጠሎ በመነሳቱ ሳቢያ ምክንያት አውሮፕላኖቹን ለመላክ እንዳልቻለ መግለጹን የኢትዮጵያ የዱር እንሰሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል።
 
ዳይሬክተሩ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት አምባ በሚባለው የፓርኩ አካባቢ ያለውን እሳትን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። ያም ሆኖ ወደ ስምጡ የፓርኩ ክፍል የተዛመተውን እሳት ግን እስካሁን መቆጣጠር አልተቻለም ነው ያሉት።
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami