Uncategorized

ፌዴራል ፖሊስ በሙስናና በኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀሎች  የጠረጠራቸውን 61 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አዋለ

ፌዴራል ፖሊስ በሙስናና በኢኮኖሚ አሻጥር ወንጀሎች  የጠረጠራቸውን 61 የመንግስት ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር አዋለ።

ከታሳሪዎቹ መካከል የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባ ይገኙበታል ተብሏል።

አዲስ ፎርቹን ድረገጽ እንደዘገበው ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን  በቁጥጥር ስር ያዋለው ከትናንት ማለዳ ጀምሮ ባካሄደው ዘመቻ ነው።

በቁጥጥር ሰር ከዋሉት ባለስልጣናት ውስጥ የቀደመው የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር፣ የግዢና ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ አገልግሎት፣ የምግብና መድሃኒት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍና አቅርቦት ኤጀንሲ እንዲሁም የኢትዮጵያ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የስራ ሃላፊዎች ይገኙበታል ተብሏል።

የጠቅላይ ዐቃቢህግ ቢሮ ይህንን አስመልክቶ ዛሬ ማምሻውን መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami