Politics

የፖለቲካ ፓርቲዎች  ለሚያቋቁሙት የጋራ ምክርቤት የውስጥ ስራ አፈፃፀም ደንብ ላይ ከምርጫ ቦርድ ጋር እየተወያዩ ነው

የፖለቲካ ፓርቲዎች  ለሚያቋቁሙት የጋራ ምክርቤት የውስጥ ስራ አፈፃፀም ደንብ ላይ ከምርጫ ቦርድ ጋር እየተወያዩ ነው

የፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫቦርድ ጋር ተወያይተው መጋቢት 5ቀን 2011 ዓ.ም በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት እና በተናጠል የሚያደርጓቸውን እንቅስቃሴዎች የሚገዛ የአሰራር ስርአት የቃልኪዳን ሰነድ  ገዢው ፓርቲን ኢህአዴግን ጨምሮ ሌሎችም ሰነዱ ላይ የተስማሙ ፓርቲዎች መፈራረማቸው ይታወቃል፡፡

ይህን የቃልኪዳን ሰነድ የፈረሙ ፓርቲዎች ሰነዱን የሚያስፈፅም ደንብ እና ሰነዱን በፈረሙበት ወቅት በተስማሙት መሰረት የፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት የውስጥ የስራ አፈፃፀም ደንብ ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

የሚያቋቁሙት  የጋራ ምክርቤት ውስጥ ስራ አፈፃፀም ደንቡ የም/ቤቱ ስራ አመራር፣ የምክር ቤቱ ስብሰባዎች፣ የም/ቤቱ ሰብሳቢዎች እና ሌሎችም ሃላፊነቶች፣ እንዲሁም የአባላት ቁጥርን የሚመለከቱ ደንቦች በማስፈፀሚያው ተካትተዋል፡፡

ውይይቱ ነገም የሚቀጥል ሲሆን በዛሬው ውሏቸው የፖለቲካ ፓርቲዎችየጋራ ም/ቤት ማስፈፀሚያ እና ባለፈው ጊዜ ተስማምተው ያፀደቁት የቃል ኪዳን ሰነድ ማስፈፀሚያ ደንብ ማሻሻያዎች ላይ ተወያተው የምክር ቤቱን የስራ ሃላፊዎች እንደሚመርጡ ይጠበቃል፡፡

ከምርጫ ቦርድ ጋር በቀጣይ ቀን በሚኖረው ውይይት ደግሞ ፓርቲዎቹ የምርጫ ህጉ ማሻሻያዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ሰምተናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami