የሱዳን ጊዜያዊ መንግስት አልበሽርን አሳልፌ አልሰጥም አለ፡፡
አልበሽርን ከልጣን አስወግዶ ሀገሪቱን ለሁለት ዓመታት ለመምራት የተቋቋመው ወታደራዊ ምክር ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሰሩት ለተባለው ወንጀል በሀገራቸው ይዳኛሉ እንጂ ለየትኛውም ሀገር ተላልፈው አይሰጡም ብሏል፡፡
አልበሽር እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2008 እና 2009 በሱዳን ዳርፉር የጦር ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ ቆርጦባቸው ነበር፡፡
ይሁን እንጂ አልበሽርን አሳልፎ ለሌላ ሀገር መስጠት ለሱዳን ስም የማይመጥን በመሆኑ ይህን አናደርግም ነው ያለው ምክር ቤቱ፡፡
መንገሻ ዓለሙ