ኢቫንካ ትራምፕ በአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸዉን ላጡ ዜጎች የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ሐዘናቸውን ገለፁ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልጅና ከፍተኛ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ ኢቫንካ ትራምፕ በኢትዮጵያ እያካሄዱት ባለው ጉብኝት በሳለፍነው ወር ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸዉን ላጡ ሐዘናቸዉን ገልጸዋል፡፡
ኢቫንካ ትራምፕ ዛሬ ጠዋት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ሄደዉ ነዉ ሐዘናቸውን የገልጹት፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ እየተጓዘ የነበረው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በመከስከሱ የ157 ተጓዦች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል ፡፡
ዘገባዉ የአፍሪካ ኒዉስ ነዉ፡፡