የኢኳዶር አሳንጄን ያባረርኩት በኢምባሲየ ተቀምጦ እየሰለለ ስላስቸገረኝ ነው አለች፡፡
ኢኳዶሩ ፕሬዝዳንት ሌኒን ሞሬኖ የዊክሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ ጥያቄውን ተቀብለን ጥገኝነት ብንሰጠውም እሱ ግን ኢምባሲያችንን የስለላ ማእከል ሊያደርገው ሞክሯል ብለዋል፡፡
ቤታችንን የስለላ ማእከል አናደርግም ስንል እንዲሁ በመላ ምት ሳይሆን ትክክለኛ ማስረጃ ይዘን ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ የአሳንጄ ድርጊት በዓለም አቀፉ ህግ መሰረት ጥገኝነትን ያሳጣል ብለዋል፡፡
የጁሊያን አሳንጄ ጠበቃ ጀኒፈር ሮቢንሰን በበኩላቸው ደንበኛቸው ከኢኳዶር ፕሬዝዳንት የቀረበበትን ክስ ውድቅ አድርገዋል፡፡
ጠበቃዋ አሳንጄ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ የሚለውን ጥያቄ እስከ መጨረሻው እንደሚቃወሙም ተናግረዋል፡፡
የእንግሊዝ ፖሊስ አሳንጄን በቁጥጥር ስር ያዋልኩት ኢኳዶር ከኢምባሲዋ እንዳባረረችው ካረጋገጥኩ በኋላ ብለዋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ