EthiopiaSportSports

በቦስተን ማራቶን ኢትዮያዊቷ አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ አሸንፋለች

በIAAF የወርቅ ደረጃ የተሰጠው በአሜሪካ የሚካሄደው የቦስቶን ማራቶን 2019 ውድድር በትናንትናው ዕለት ለ15ኛ ጊዜ ተካሂዷል፡፡

በውድድሩ በሴቶች የተደረገውን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ ቦስተን ላይ የሮጠችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ ከውድድሩ 5 ኪ.ሜ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ ብቼዋን ሩጣ 2፡ 23፡ 31 በሆነ ጊዜ ቀዳሚ ሁና ጨርሳለች፡፡

ኬንያዊቷ ኤድና  ኪፕላጋት 2፡ 24፡ 13 ጊዜ ሁለተኛ ስትሆን፤ አሜሪካዊቷ ጆርዳና ሃሳይ በ2፡ 25፡ 20 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡ አትሌት መስከረም አሰፋ በ2፡ 25፡ 40 አራተኛ ደረጃ ወጥታለች፡፡

ብርቱ ትንቅንቅ በነበረው የወንዶች ፉክክር ደግሞ ኬንያዊው ላውረንስ ቼሮኖ ኢትዮጵያዊውን አትሌት ደሲሳ ሌሊሳ በመቅደም 2፡ 07፡ 57 በመግባት ለመጀመሪያ ጊዜ በተወዳደረበት ውድድር አሸናፊ ሁኗል፡፡

የውድደሩ ሁለት ጊዜ ባለድል አትሌት ደሲሳ ሌሊሳ በሁለት ሰከንዶች ዘግይቶ 2፡ 07፡ 59 ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ ኬንያዊው ኬኔዝ ኪፕኬሞይ በ2፡ 08፡ 07 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሷል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami