EthiopiaSportSports

የባየርን ሙኒክ ከ17 ዓመት በታች ወጣቶች እግር ኳስ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ በአዲስ አበባ የሚከፍተውን የእግር ኳስ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት አስመልክቶ የአንድ ቀን የእግር ኳስ ውድድር በሚል በአዲስ አበባ በሚገኙ 8 ክለቦች መካከል የ17 ዓመት በታች ወጣቶች የሚሳተፋበት እግር ኳስ ውድድር ዛሬ ከጠዋቱ 3፡30 – 8፡00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሂዳል፡፡

ውድድሩ በስምንት ክለቦች መካከል በሁለት ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ሲሆን፤ በምድብ ሀ፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ሠላም እግር ኳስ ክለብ ሲገኙ፤ በምድብ ለ፡ ኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ሠውነት ቢሻው እግር ኳስ ቡድን፣ ደደቢት እግር ኳስ ክለብ፣ ኢትዮጵያ መድን ይወዳደራሉ፡፡

የጨዋታው አሸናፊ ክለብ የዋንጫ እንዲሁም ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ሁነው ለሚጨርሱ ቡድኖች ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡

በኘሮግራሙ ላይ የክብር እንግዶች፣ የባየርሙኒክ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የስፖርት ከፍተኛ አመራሮች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ ለሚከፈተው የእግር ኳስ ማሠልጠኛ የተዘጋጀው የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

                                                                                                                        ምንጭ፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami