የጀርመኑ ሀያል የእግር ኳስ ክለብ ባየርን ሙኒክ በስሙ የሚጠራውን እና በአፍሪካ የመጀመሪያውን የእግር ኳስ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ከፍቷል፡፡ የትምህርት ቤቱን መከፈት ተከትሎ ክለቡ በአለም ላይ የከፈታቸውን ተመሳሳይ የእግር ኳስ ማስተማሪያ ተቋማቱን ስድስት ያደርሰዋል ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል ክለቡ የእግር ኳስ ትምህርት ቤቶቹን በአሜሪካ፤ ቻይና፤ ታይላንድ፤ ጃፓን እና ሲንጋፖር መክፈት ችሏል፡፡
በኢትዮጵያ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙትና የባየር ሙኒክ ክለብ መገኛ የሆነችው የባቫሪያ ግዛት ሚኒስትር- ፕሬዝደንት ማርከስ ሶደር “ሣህለ ወርቅ I “ የሚል ጹሁፍ የተጻፈበትን የክለቡን ማልያ ለፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በስጦታነት አበርክተዋል፡፡
መረጃው፡ የፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ነው