Global TradeWorld News

ሰሜን ኮሪያ በቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ እንድትሳተፍ ከቻይና ግብዣ ቀረበላት፡፡

ሰሜን ኮሪያ በቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ እንድትሳተፍ ከቻይና ግብዣ ቀረበላት፡፡

ቻይና ግዙፍ ኢኮኖሚን ለማንቀሳቀስ ያስችላል ተብሎ የታመነትን አንድ ቀበቶ አንድ መንገድ የሚል ስያሜ የተሰጠውን ፕሮጀክት አስመልክታ በሚቀጥለው ሳምንት ጉባኤ ታካሂዳለች፡፡

ቤጂንግ በአንድ ትሪሊዮን ዶላር በጀት በምትገነባው በዚህ ፕሮጀክት ሀገራት እንዲሳተፉበት ተደጋጋሚ ጥሪ ስታቀርብ ቆይታለች፡፡

ፕሮጀክቱን በአንዳንድ ሀገራት የተጋነነ ተስፋ የተጣበት ነው በማለት ይተቹታል፡፡ አሜሪካ እና አውሮፓንም በሀሳብ ለሁለት ከፍሏል ነው የተባለው፡፡

ጣሊያን ከቡድን 7 ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ ይህን ፕሮጀክት የተቀላቀለች ሀገር ሆና ተመዝግባለች፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በአሁኑ የቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ ከ37  ሀገራት በላይ በመሪዎች ደረጃ የሚሳተፉበት ሲሆን ሰሜን ኮሪያም የጉባኤው ታዳሚ እንድትሆን ቻይና ጋብዛታለች፡፡

የቻይና የቅርብ ጎረቤት የሆነቸው ሰሜን ኮሪያም በጉባኤው ላይ የሚሳተፍ ተወካይዋን ወደ ስፍራው እንደምትልክ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ጉባኤ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል የሚበዙት የቀድሞዋ ሶቬት ህብረት አጋሮች የነበሩ የደቡብ እስያ እና የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት እንደሆኑ ዘገባው ያሳያል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

 

 

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami