SportSports

ፒ. ኤስ . ጂ የፈረንሳይ ሊግ አንድ አሸናፊ መሆኑን አረጋገጠ

የፈረንሳይ ሊግ አንድ የ33ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ተካሂደዋል፡፡
በትናንትናው ዕለት ፓሪስ ሴንት ዤርማ ፓርክ ደ ፕሪንስ ላይ ሞናኮን 3 ለ 1 በመርታት ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል፡፡ ወጣቱ ፈረንሳያዊ ተጫዋች ክሊያን እምባፔ ሶስቱን ጎሎች ከመረብ በማገናኘት ሀትሪክ መስራት ችሏል፡፡ እምባፔ በአንድ የሊጉ የውድድር ዓመት ብቻ 30 ጎሎችን በማስቆጠር የመጀመሪያው ወጣት ተጫዋች ነው፡፡


አሌክሳንደር ጎሎቪን የሞናኮን ግብ አስገኝቷል፡፡
ፒ . ኤስ. ጂ የሊጉ አሸናፊ መሆኑን ያረጋገጠው ከመጫወቱ በፊት ሲሆን ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሊል ከቱልዝ ጋር ያለግብ አቻ መለያየቱን ተከትሎ ነው፡፡

ፓሪሱ ቡድን የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ በሰባት ዓመታት ውስጥ ስድስተኛ የዋንጫ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል፡፡
የሻምፒዮኖቹ ተጫዋቾች ከማሊያቸው ጀርባ ስማቸው መፃፊያ ላይ በቅርቡ ቃጠሎ የደረሰበትን የኖትር ዳም ካቴድራንል ለማሰብ ሲሉ አስፍረዋል፡፡
ብራዚላዊው ኔይማር ዳ ሲልቫ ከጥር ወር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጉዳቱ አገግሞ በጨዋታው ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡
ፓሪስ ሴንት ዤርማ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ የፈረንሳይ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ከስታደ ሬን ጋር ያካሂዳል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami