በጅግጅጋ ቶጎ ውጫሌ የአሜሪካ ዶላርና ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ተባለ፡፡
ከገቢዎች ሚኒስቴር እንዳገኘነው መረጃ ለዛሬ አጥቢያ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-50322 ኦሮ በሆነ ተሽከርካሪ 39 ሺ 700 ዶላር ይዞ ወደ ውጪ ሃገር ሊያስወጣ የነበረ ግለሰብ በቶጎ ውጫሌ የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያዝ ችሏል ፡፡
ግለሰቡ ዶላሩን በጥቁር ፕላስተር ከጠቀለለ በኋላ በሁለቱም እግሮቹ ቡትስ ጫማዎች ውስጥ እንደገበር አድርጎ ሊያሻግር ሲሞክር ነው የተያዘው ተብሏል፡፡
ገንዘብ እንደ ጫማ ገበር ተደርጎ ሊወጣ ሲል በዚሁ ኬላ ላይ ለ3ኛ ጊዜ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስነብቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳ ለዛሬ አጥቢያ ሌሊት በተመሳሳይ ሰዓት በዚሁ ኬላ 41 የማካሮቭ ጥይቶችን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-54157 ኦሮ መኪና ደብቆ ሊያስወጣ የሞከረ ሌላ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተሰምቷል፡፡