AfricaPolitics

የአፍሪካ መሪዎች  በሱዳን እና በሊቢያ ጉዳይ ለመምከር ግብፅ ላይ ተገናኝተዋል፡፡

የአፍሪካ መሪዎች  በሱዳን እና በሊቢያ ጉዳይ ለመምከር ግብፅ ላይ ተገናኝተዋል፡፡

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ በመሩት አስቸኳይ ስብሰባ የመጀመሪያ አጀንዳ ያደረገው የሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ነው፡፡

በሊቢያ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ የሚቆምበትን መፍትሁ ማፈላለግም መሪዎቹ የሚመክሩበት ሌላኛው አጀንዳ ነው፡፡

አልሲሲ ከደቡብ አፍሪካው አቻቸው ሲርል ራማፎሳ ጋር በግል በተወያዩበት ወቅት በአፍሪካ አህጉር ችግር ሲፈጠር የሚፈታበት መንገድ በጠንካራ መርህ ላይ የተመረሰተ እንዲሆን አንድ ወጥ የሆነ አሰራር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሺን ዋና ፀሀፊ ሙሳ ፋቂ መሃማት በካይሮው ስብሰባ ከኢትዮጵያ፣ ከደቡበ ሱዳን፣ ከዩጋንዳ፣ ከኬንያ እና ናይጀሪያ የተውጣጡ ባለ ስልጣናት ጋር እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣኑን በ15 ቀናት ውስጥ ለሲቪል ካላስረከበ ሀገሪቱን ከህብረቱ አባልነት እንደሚሰርዝ ማጠንቀቁ ይታወሳል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami