የ2011 የአለም የወባ ቀንን በማስመልከት የተዘጋጀው ፕሮግራም በድሬደዋ ተጀመረ።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ሰለሞን እንደገለፁት በአለም አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን የወባ ማጥፋት ዘመቻ የተቀላቀለችው ኢትዮጵያ በስድስት ክልሎችና 239 ወረዳዎች የዘረጋችው መርሀ ግብር ውጤታማ መሆኑ ተነግሯል
የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ፉአድ ከድር በበኩላቸው ከአሁን ቀደም በድሬደዋ ነዋሪዎች በእለት ተእለት ኑሮ ላይ ጫና ሲፈጥር የነበረውን የወባ በሽታ መከላከል መቻሉን ገልፀው ህብረተሰቡ በቀጣይም በዚህ ረገድ ተግቶ ተግባሩን እንዲቀጥል የግንዛቤ ማስጨበጡ ስራ መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡
እስከመጪው ሀሙስ በሚኖሩት ቀናት በፕሮግራሙ ከመስክ ጉብኝት በተጨማሪ የወባ ቀንን በማስመልከት የተዘጋጁ የተላያዩ ጉዳዮች ይከወኑበታል፡፡
መረጃው የጤና ሚኒስቴር ነው