SportSports

የኮፓ ኢታሊያ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ እና ነገ ይደረጋሉ

የጣሊያን ኮፓ ኢታሊያ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያ፤ ከወር በፊት በእስታዲዮ ኦሊምፒኮ ላትሲዮ ከኤስ ሚላን ያለግብ በአቻ ውጤት እንዲሁም ፊዮረንቲና በአርቴሚዮ ፍራንኪ ስታዲም ከአታላንታ በ3 ለ 3 አቻ ውጤት መለያታቸው ይታወሳል፡፡

የመልስ ጨዋታዎች ደግሞ ዛሬ እና ነገ ምሽት ሲከናወኑ በዛሬው ዕለት ምሽት 3፡45 ላይ ኤስ ሚላን በስታዲዮ ጁሴፔ ሚያዛ የሮማውን ከተማ ቡድን ላትሲዮ ያስተናግዳል፡፡ የሚላኑ ቡድን ከሜዳው ውጭ አድቫንቴጅ ይዞ መመለሱ በምሽቱ ተጠቃሚ ያደርገዋል ተብሏል፡፡

ሁለቱም ቡድኖች ከጣሊያ ሴሪ ኤው ውድድር ሲመለሱ ኤስ ሚላን ከፓርማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ባለቀ ሰዓት በፍራንክ ኬሲ የፍፁም ቅጣት ምት ጎል አቻ መሆን ሲችል፤ ላትሲዮ ደግሞ በሜዳው እና ደጋፊው ፊት በሊጉ ግርጌ ላይ በሚገኘው ኬቮ የ2 ለ 1 ሽንፈት ገጥሞታል፡፡

ዛሬ ወደ ፍፃሜ ዋንጫ ጉዞ እያለሙ ሲጨወቱ፤ በባለሜዳው ቡድን በኩል ግብ ጠባቂው ጃንሊጂ ዶናሩማ ከመጠነኛ ህመም መልስ ለጨዋታው ብቁ ሲሆን ሉካስ ፓኩዬታም ይሰለፋል ተብሏል፡፡ አማካዩ ጂያኮሞ ቦናቬንቹራ እስከ የውድድር ዓመቱ ማብቂያ ድረስ በጉዳት የማይመለስ በመሆኑ ከጨዋታው ውጭ ሁኗል፡፡

የላትሲዮው አማካይ ሰርጂ ሚሊንኮቪች ሳቪች ከኬቮ ጋር በነበረው ጨዋታ የቀይ ካርድ ሰለባ የሆነ ቢሆንም፤ የሴሪ ኤው ቀይ ካርድ በኮፓ ኢታሊያ የማይተገበር በመሆኑ ለቡድኑ አስፈላጊውን ግልጋሎት ለመስጠት ዝግጁ ነው ተብሏል፡፡

ነገ ምሽት ቤርጋሞ ላይ በአትሌቲ አዙሪ ደ ኢታሊያ አታላንታ ከፊዮረንቲና ይፋለማሉ፡፡የደርሶ መልስ ግጥሚያዎች አሸናፊዎች ለዋንጫ ጨዋታ የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami