SportSports

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 36ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬን ጀምሮ ይካሄዳል

የዘንድሮው የሊጉ መርሀግብር ሊጠናቀቅ የሶስት ጨዋታዎች ዕድሜ የቀሩ ሲሆን የሊጉ አሸናፊ እና የቀጣይ ዓመት የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፊ ለመሆን የሚደረገው ፉክክር አጓጊነት በርትቷል፡፡

ዛሬ በሳምንቱ መርሀግብር ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ከሊጉ የተሰናበተውን ሀደርስፊልድ ታውን ምሽት 4፡00 ሰዓት ሲል ያስተናግዳል፡፡

ቀያዮቹ የተቀናቃኛቸውን ማንችስተር ሲቲ ነጥብ መጣል እየናፈቁ፤ የዛሬውን ጨዋታ ጨምሮ በሌሎቹ አሸናፊነታቸውን አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል፡፡

ነገ የሳምንቱ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ቀን 8፡30 ቶተንሃም ሆተስፐር በለንደን ደርቢ ዌስትሃምን ሲገጥም ፤ አመሻሽ 11፡00 ላይ በተመሳሳይ ሰዓት አራት ያህል ግጥሚያዎች ይደረጋሉ፡፡

 ክሪስታል ፓላስ ከኢቨርተን፣ ፉልሃም ከካርዲፍ ሲቲ፣ ሳውዛምፕተን ከቦርንመዝ እና ዋትፎርድ ከወልቭስ ይገናኛሉ፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ብራይተን ከኒውካስትል ይጫወታሉ፡፡

ዕሁድ አርሰናል ወደ ኪንግ ፓወር አምርቶ ሌስተርን ይጎበኛል፤ የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ በቱርፍ ሞር ከበርንሊ ጋር ይፋለማል፡፡

የሳምንቱ ተጠባቂ ግጥሚያ በማንችስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ መካከል በኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም ምሽት 12፡30 ላይ ይደረጋል፡፡

ማንችስተር ሲቲ ሊጉን በ89 ነጥቦች እየመራ ይገኛል፤ ሊቨርፑል በ88 ነጥብ ይከተላል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami