ሱዳናዊያን ካርቱም በሚገኘው የግብፅ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሟቸውን ገለፁ፡፡
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር አብደልፈታህ አልሲሲ በመሩት ስብሰባ የአፍሪካ መሪዎች ካይሮ ላይ ያሳለፉት ውሳኔ ነው የተቃውሞ ሰልፈኞቹን ለዚህ ተቃውሞ ያነሳሳቸው፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ህብረቱ የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣኑን ለሲቪል የሽግግር መንግስት ለማስረከብ የሰጠውን የ15 ቀናት ቀነ ገደብ ወደ 3 ወር ማራዘሙ በሱዳናዊያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡
ሰልፈኞቹ ውሳኔውን ቀጥታ ከአልሲሲ ጋር በማያያዝ በግብ አቅራቢያ ተሰባስበው አልሲሲ ሆይ ይህ ሱዳን ነው፤ የእርስዎ ድንበር እስከ አስዋን ድረስ ነው በማለት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሲጮሁ ተሰምተዋል፡፡
ከአሁን ቀደም በርካታ የዓለም ሀገራት ሱዳን በወታደራዊ አገዛዝ ስር ወደቀች ብለው ትችት ሲሰነዝሩ አልሲሲ ወታደራዊ ምክር ቤቱ ሀገሪቱን በተረጋጋ መንገድ እንደሚመራት እምነት አለኝ በማለታቸውም ሱዳናዊያኑ ቂም ይዘውባቸዋል ተብሏል፡፡
መንገሻዓለሙ