SportSports

ቼካዊው ጆሴፍ ሱራል በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ

አደጋው የደረሰው በትናንትናው ዕለት ሲሆን የቱርኩ አይቴሚዝ አልያንስፖር ከካያሴሪስፖር ጋር የነበረውን የቱርክ ሊግ ጨዋታ አጠናቀው እየተመለሱ በነበረበት ወቅት የክለቡ መቀመጫ በሆነችው የደቡብ ጠረፍ ከተመዋ አላንያ አምስት ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሚገኝ ስፍራ፤ የቡድኑን ስብስብ የያዘው ባስ ተገልብጦ የ28 ዓመቱ ቼካዊው አጥቂ ጆሴፍ ሱራል ወደ ሆስፒታል ከሄደ በኋላ ህይወቱ አልፏል፡፡

ስድስት የበድኑ አባላት ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሆስፒታል ይገኛሉ፡፡

የክለቡ ሰባት ተጨዋቾች በግል ኪራይ ላይ በተያዘችው ሚኒ ባስ ላይ ነበሩ፡፡

የክለቡ ሊቀመንበር ሀሰን ካቩሶግሉ ሚኒ ባሷን እያሽከረከረ የነበረው ሹፌር እንቅልፍ ጥሎት እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

አደጋው በተከሰተበት ወቅት የሹፌሩ ረዳትም ቢሆን እንቅልፍ ላይ እንደነበረ ተግልጧል፡፡

ክለቡ በትዊተር ገፁ እንዳሰፈረው በደረሰው አደጋ እና በጆሴፍ ሱራል የደረሰውን ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልፆል፡፡

የቀድሞው የስፐርስ፣ ካርዲፍ እና ኪው.ፒ.አር ተከላካይ ስቴቨን ካውከር እና የቀድሞው የኒውካስትል አጥቂ ፓፒስ ሲሴ በአላንስፖር ክለብ ይገኛሉ፡፡

ካውከር ደግሞ ቡድኑ ከኬይሴሪስፖር ጋር በነበረው ጨዋታ የአቻነቷን ጎል ከመረብ ያገናኘ ሲሆን እርሱ አሊያ ሲሴ ከሚኒ ባሷ ውስጥ ተሳፍረው ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል ስለመኖራቸው እና አለመኖራቸው ምንም የተባለ ነገር የለም፡፡

ሌሎች የቡድኑ ተጫዋቾች እና የክለቡ አባላት የክለቡ ንብረት በሆነው  ባስ ላይ ነበሩ፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami