ፈርዲናንድ የማንችስተር ዩናይትድ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ለመሆን በዕጩነት ቀርቧል ተብሏል፡፡
የቀድሞው የቀያይ ሰይጣኖቹ ታላቅ ተከላካይ ሪዮ ፈርዲናንድ የክለቡ ስፖርቲነግ ዳይሬክተር ለመሆን በሚደረገው ጥረት የቀዳሚውን ደረጃ ይዟል ሲል ዴይሊሜል አስነብቧል፡፡
ፈርዲናንድ ከማንችስተር ዩናይትድ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ኢድ ውድዋርድ ጋር እየተወያየ ስለመሆኑ የተነገረ ሲሆን የክለቡ ባለቤቶች የሆኑት የግሌዘር ቤተሰቦች፤ ጡረታ የወጣውን ተከላካይ ወደ ሀላፊነት ለማምጣት ፍላጎት እንዳላቸው እና የአራት ዓመት ውልም የማሰር ውጥን እንዳላቸው ተነግሯል፡፡
ውድዋርድ የቀድሞው ተጫዋች ፈርዲናንድ ለስፖርቲንግ ዳይሬክተርነት ሚና ብቁ እንደሆነ እንደሚያምኑ የተጠቆመ ሲሆን ከዩናትድ ጋር የሰራቸው ታሪኮች እና በበዝነስ ዓለም ያለው ልምድ ደግሞ ለዚህ ያግዘዋል ተብሏል፡፡
……………………………
ኦክስሌድ ቻምበርሊን ለዓዲስ ስምምነት መቃረቡ ተነግሯል
የሊቨርፑል ተጨዋች የሆነው እንግሊዛዊው አሌክስ ኦክስሌድ ቻምበርሊን፤ ለአንድ ዓመት ያህል ጉዳት ላይ ከነበረ በኋላ ከሀደርስፊልድ ጋር በነበረው ጨዋታ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገና ሲሆን ከመርሲ ሳይዱ ቡድን ጋር አዲስ የስምምነት ፊርማ ለማድረግ እየተነጋገረ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ቻምበርሊን ተጨማሪ የ12 ወራት ውል ለማሰር እየተነጋገረ ሲሆን ይህ ማለት ደግሞ ተጫዋቹ እስከ 2023 ድረስ በቀያዮቹ ቤት ያቆየዋል ማለት ነው፡፡
……………………………
ፓሪስ ሴንት ዤርማ ለዴ ሂያ ይፋዊ ጥያቄውን ሊያርብ እንደሆነ ተነግሯል
የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ዤርማ ክለብ ለማንችስተር ዩናይትዱ ግብጠባቂ ዳቪድ ዴ ሂያ 90 ሚሊዮን ዩሮ በማቅረብ ጥያቄውን እንደሚያቀርብ ዴይሊ ስታር ዘግቧል፡፡
ስፔናዊው ግብ ጠባቂ አሁን ላይ በማንችስተር ዩናይትድ በሳምንት 200 ሺ ፓውንድ የሚከፈለው ሲሆን የፓሪሱ ቡድን ወደ 450 ሺ በማሻደግ የረዥም ጊዜ ውል ሊያቀርብለት እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ተጫዋቹ በቅርብ ክለቡ ባደረጋቸው ጨዋታዎች የሚቆጠሩበት ጎሎች እያሳጡት በመሆኑ እና ጫናው በመበርታቱ ወደ ሌላ ክለብ እንዲመለከት እንደሚያስገድደው እየተነገረ ነው፡፡
……………………………
አሰልጣኝ ጋስፔሪኒ ለኤስ ሚላን ሀላፊነት ስማቸው እየተነሳ ነው
ጂያን ፔዬሮ ጋስፔሪኒ ለጣሊያኑ ክለብ ኤስ ሚላን አሰልጣኝነት ከታጩት እና የአሁኑን የቡድኑን አሰልጣኝ ጂናሮ ጋቱሶ ሊተኩ ይችላሉ ተብሎ ከሚጠበቁት መካከል አንዱ እንደሆኑ ላ ጋዜጣ ዴሎ ስፖርት አስነብቧል፡፡
እኝህን የአታላንታ አሰልጣኝ የሮዘነሪዎቹ ሀላፊ ለማድረግ ፓውሎ ማልዲኒ እየመከረ ነው ተብሏል፡፡
………………………………..
ሌላኛው የሚላን ክለብ ኢንተር ሚላን ደግሞ በሚቀጥለው የውድድር ዓመት ከአዲስ አሰልጣኝ ጋር ሊመጣ እንደማይችል ተነግሯል፡፡
ኢንተር ክለቡን እያሰለጠኑ ከሚገኙት ሉሽያኖ ስፓሌቲ ጋር በሚቀጥለው ዓመት ላንመለከታቸው እንችላለን፤ እንዳውም ክለቡ ለእሳቸው ተተኪ እንዲሆን አዲስ ሰው እየተመለከቱ እንደሆነ በሰፊው ቢወራም፤ የኢንተር ሚላን ክለብ ዋና ስራ አስኪያጅ ጁሴፔ ማሮታ ስፓሌቲ በሀላፊነታቸው ይቀጥላሉ ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፡ ጎል ዶት ኮም