ኢትዮጵያ እና ኬንያ ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸውን ይበልጥ ማጠናከር አለባቸው ሲሉ የኬንያዉ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ገልጸዋል።
በኬንያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ትናንት ከኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር የሁለቱን አገሮች የኢኮኖሚ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙረያ ተወያይተዋል።
በነበረው ውይይት ሁለቱ አገሮች ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የህዝበ ለህዝብ ግንኙነታቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የኢኮኖሚ ትስስሩን ማሳደግ አለባቸው ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስር ማዘመንና ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ነው ዶ/ር ዊለያም ሩቶ የገለጹት፡፡
የ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ሁለቱ አገሮች በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በተለይም በቆዳ ኢንዱስትሪ በትብብር በመስራት ለዜጎች የስራ እድል መፍጠርና ኢኮኖሚውን የማሳደግ ስራ ላይ አትኩረው እንደሚሰሩ በነበረው ውይይት መግባባት ላይ ደርሰዋል።