EthiopiaSportSports

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት አደረጉ::

በትናንትናው ዕለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ አንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ዘሪሁን ቀቀቦ ከክልሉ የባህል እና ስፖርት እንዲሁም የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንትን በሀዋሳ በመገኘት የሲዳማ እና የወላይታ ዲቻ ክለቦች በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምክንያት ጨዋታዎቻቸውን በገለልተኛ ሜዳ እያደረጉ መሆኑ እንዲሁም ከግዜ ወደ ጊዜ ይህ ችግር ወደ ሌሎች ክለቦችም እየተዛመተ መሆኑ በ21ኛ ሳምንት ጨዋታ ደቡብ ፖሊስ ከወላይታ ዲቻ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በደጋፊዎች መካልከል በነበረው ግጭት ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን በተመለከተ መፍትሄ ለማፈላለግ እና የሁለቱን ህዝቦች ለማቀራረብ በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ነጥቦች ላይ የጋራ ምክክር ተካሂዷል።

ውይይቱም ውጤታማ እና በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ ትልልቅ የውይይት መድረኮች የክለቦቹ ደጋፊ ማህበራት እና የየክለቦቹ አመራሮች ብሎም የጸጥታ አካላት በተገኙበት በወላይታ እና በሃዋሳ ውይይት በማድረግ ችግሩን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅረፍ ቃል ገብተዋል።

በቀጣይ መሰል ውይይቶችን ክልሉ አጠናክሮ በመቀጠል የህዝብ ለህዝብ ቅርርቡን ለማጠናከር እንደሚሰራ እና እግር ኳስ የተራራቀውን ህዝብ ማገናኛ ድልድይ እንጂ ማራራቂያ ሊሆን እንደማይገባ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ቀደም ጨዋታቸውን በገለልተኛ ሜዳ ያካሂዱ የነበሩትን የትግራይ እና የአማራ ክልል ክለቦች እንዲሁም የክልል ሀላፊዎች እና የደጋፊ ማህበራት የፌዴሬሽን ጥያቄን በመቀበል በሜዳቸው ጨዋታቸውን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami