የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የዉጭ ዜጎች በባንክ ዘርፍ ዉስጥ መሳተፍ እንዲችሉ የሚያደርገዉ ረቂቅ አዋጅ እንዲጸደቅ ለተወካዮች ምክርቤት ተላክ
የሚኒስትሮች ምክርቤት የባንክ ስራን ለማሻሻል የቀረበዉን ረቂቅ አዋጅ በመመርመር ነዉ ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አዋጁ እንዲጸድቅ የላከዉ፡፡
የሚኒስትሮች ምክርቤት ትላንት ባካሄደዉ 15ኛዉ አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የዉጭ ዜጎች በባንክ ዘርፍ ዉስጥ መሳተፍ እንዲችሉ ማድረግ ፤ባንኮች ከሀገርዉስጥም ሆነ ከዉጭ ሀገር ባንኮች ገንዘብ በማሰባሰብ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ልማት ከፍተኛ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግና ባንኮች በሀገሪቱ ዉስጥ የኢኮኖሚ የክፍያ ስርዓትና የክፍያ አፈጻጸም ዉስጥ ላቅ ያለ ሚና ስላላቸዉ ከፍ ማድረግ ላይ ዉይይት ተደርጓል፡፡ ብሄራዊ ባንክ ረቂቅ አዋጁን ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበ ሲሆን ፤የምክርቤቱ አባላትም በጉዳዮቹ ላይ ዉይይት ካደረጉ በኋላ ለተወካዮች ምክር ቤት ረቂቁን ልከዋል፡፡
ከዚህም ሌላ ምክር ቤቱ ንግድ ምዘገባ አዋጅን ለማሻሻል የወጣዉን ረቂቅ፤የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን በገንዘብ ለመደገፍ ጥቅም ላይ የዋሉ ገንዘቦችን ለማገድ በወጣዉ አዋጅ ላይ ተወያይቷል፡፡
የምኒስትሮች ምክርቤት ስለ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዉሳኔ ማሳለፉንም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡