AfricaPolitics

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በሽግግር ኮሚቴው የሲቪሎች ቁጥር ይብዛ የሚለውን ጥያቄ ውድቅ አደረገው፡፡

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በሽግግር ኮሚቴው የሲቪሎች ቁጥር ይብዛ የሚለውን ጥያቄ ውድቅ አደረገው፡፡

የምክር ቤቱ አባላት እንደተናገሩት የጋራ ኮሚቴው ቀደም ሲል እኛ ባቀረብንው ሀሳብ መሰረት ካልተከናወነ አንቀበለውም ብለዋል፡፡

ቢቢሲ ሌተናል ጄኔራል ሳላህ አብደልካሌክን ጠቅሶ  እንደዘገበው ወታደራዊ ምክር ቤቱ እና አሊያንስ ፎር ፍሪደም ኤንድ ቸንጅ የተባለው ህዝባዊ አመፁን የመራው አካል በጉዳዩ ዙሪያ ቢመካከሩም መግባባት አልቻሉም፡፡

ተቃዋሚዎቹ 15 አባላት ተቋቁሞ 8 ሲቪሎች እና 7 ከጦሩ ይካተቱበት ሲሉ ምክር ቤቱ ደግሞ 10 አባላት ይበቃሉ  ሰባቱ ከእኛ ሶስቱ ደግሞ ከሲቪል ይሁኑ የሚል ሀሳብ አቅርቦ ነበር፡፡

ጄኔራሉ የኮሚቴዎቹ ቁጥር ግማሽ በግማሽ ይሁን የሚል ሀሳብ ቢቀርብላችሁ ትቀበሉታላችሁ ወይ ተብለው ሲጠየቁ “ምናልባት ሊያግባባን ይቻል” የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡

አብደልካሌክ አክለውም ሲቪሎች ይብዙ የሚለው ጉዳይ የመጨረሻው ቀይ መስመር ሊሆን አይገባውም ብለዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami