ሳይክሎን ፋኒ የተባለው አውሎ ንፋስ ህንድን ፋታ ነስቷታል፡፡
የህንድን ምሳራቃዊ የባህር ዳርቻ የመታው ይህ አውሎ ንፋስ አደገኛ ከሚባሉት አውሎ ንፋሶች መካከል የሚመደብ ነው፡፡
በሰዓት እስከ 200 ኪሎሜትር ድረስ የሚምዘገዘገው ይህ አውሎ ንፋስ እስካሁን ሁለት ሰዎችን ገድሏል ተብሏል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው የህንድ የብሄራዊ አደጋ ቁጥጥር ባለስልጣን አደጋው በተከሰተበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን በፍጥነት ለቀቀው እንዲወጡ አስጠንቅቋል፡፡
እስካሁን የህንድ መንግስት ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን ከአደጋው ለመጠበቅ ሲል ከመኖሪያቸው አንስቶ በጊዜጣዊ መጠለያ ለማስፈር ተገዷል፡፡
መንገሻ ዓለሙ