ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ካኖን ተቀብለው አነጋገሩ::
ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል::
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያሉትን ማሻሻያዎችና በቀጣናው ያላትን የሰላም አስተዋጽዖ በመግለጽ ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ጃፓንን እንዲጎበኙ የጠ/ሚር ሽንዞ አቤን ግብዣ አቅርበዋል::
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በበኩላቸው ጃፓን የኢትዮጵያ የልማት ተባባሪ መሆኗን አንሥተው በሰው ሀብት ዐቅም ግንባታ፣ በንግድና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ቀጣይ ትብብር እንዲኖር ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል::