EthiopiaPolitics

ኢትዮጵያ የሱዳንን ህዝብ ለመርዳት ቁርጠኛ መሆንዋን ገለጸች፡፡

ኢትዮጵያ የሱዳንን ህዝብ ለመርዳት ቁርጠኛ መሆንዋን ገለጸች፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን አቋሟን የገለጸችዉ  የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ጋር በተወያዩበት ወቅት ነዉ
አቶ ገዱ ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር በሱዳን ካርቱም በተወያዩበት ወቅት ኢትዮጵያ የሱዳንን ህዝብ ለመርዳት ቁርጠኛ ናት ፤በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትገባም የሱዳንን ሉዓላዊነትም ታከብራለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ በኢጋድ ሊቀመንበርነቷ በሱዳን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲካሄድ ከአፍሪካ ህብረት እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በቅርበት በመስራት አስፈላጊውን ሁሉ ታደርጋለች ብለዋል።

የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን በበኩላቸው ፤የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት ልኡካን በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶ/ር አብይ አህመድ ስለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል።

በኢትዮጵያ እና በሱዳን ህዝብ መካከል ያለው የቆየ፣ ጠንካራ፣ ታሪካዊ እና ወንድማማች ግንኙነት ተጠናከሮ እንደሚቀጥል ሙሉ እምነታቸው መሆኑን ሌተናል ጄኔራሉ መገለጻቸዉን ከዉጭጉዳይ ቃላቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami