Uncategorized

የኢፌዴሪ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በጀርመን ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተነግሯል።
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ርእስ ብሄር በመሆን በ1987 የተሾሙ ሲሆን፥ ለ7 ዓመታትም አገልግለዋል።
በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ላይ በደንቢ ዶሎ የግል ተወዳዳሪ በመሆን ፓርላማ መግባታቸውም ይታወሳል።
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ከወጣትናቸው እድሜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲዘረጋ ሲደረግ በነበረው ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው።
ለዚህም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመሰለፍም የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ ቆይተዋል።
በታሪክ ትምህረት ሶስተኛ ወይም ዶክትሬት ዲግሪያቸውን የያዙት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፥ እንደ ምሁርነታቸው በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራትም የተለያዩ ግልጋሎቶችን ሲሰጡ ቆይተዋል።
በተማሩት ትምህርትም የኦሮሞን ባህል፣ ታሪክ እና እሴት የሚያንፀባርቁ እና የኢትዮጵያን አንድነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ጥናቶች አካሄደዋል ።

ምንጭ ፦ፋና

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami