ከ1963 ጀምሮ በየዓመቱ ሲካሄድ የነበረው ይህ ውድድር ዘንድሮ ለ48ኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከሚያዚያ 29- ግንቦት 4/2011 ዓ/ም በ36 ክለቦችና ተቋማት መካከል ሲደረግ በአጠቃላይ 1376 አትሌቶች ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁሉንም የአትሌቲክስ የውድድር ተግባራት በመካተት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የውድድሩ ዓላማ በአገር ውስጥ የውድድር ዕድል መፍጠር ፤ በክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና ክለቦች እንዲሁም ተቋማት መካከል የአትሌቲክስ ፉክክር መፍጠር፣ ለብሔራዊ ቡድን አትሌቶች ለመምረጥ እና ለዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሚኒማ ሊያሟሉ የሚችሉ አትሌቶችን በዕጩነት ለመምረጥ የሚል ነው፡፡
የውድድሩ አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች፣ ከአንዴ በላይ የወርቅ ሜዳሊያ ለሚያስመዘግቡ እና በቡድን ውጤት ለሚያስመዝግቡ አትሌቶች አንዲሁም ክብረወሰን ለሚያሻሽሉ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ይኖራል ተብሏል፡፡
ከ2.1 ሚሊየን ብር በላይ በጀት የተያዘለት ይህ ሻምፒዮና አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እንደተደረገ ተገልጧል፡፡