EthiopiaHealth

ባህላዊ  ህክምናን ጨምሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ና ስነ ምግባር ላይ የሚያተኩረዉ  አራተኛው አመታዊ የጤና ሳይንስ ጉባኤ እየተካሄደ ነዉ፡፡

ባህላዊ  ህክምናን ጨምሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ና ስነ ምግባር ላይ የሚያተኩረዉ  አራተኛው አመታዊ የጤና ሳይንስ ጉባኤ እየተካሄደ ነዉ፡፡
ለአራት ቀን በሚካሄደዉ ጉባኤ የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ፤ በጤና ፖሊሲ ክለሳ፤ ተላላፊ በሽታዎች፤የላብራቶሪ አገልግሎት እና ድንገተኛ ህክምና አሰጣጥን አስመልክቶ ለሚሻሻሉ ስራዎች መነሻ ሀሳብ ያሳያል፡፡

አራተኛውን የጤና ሳይንስ ጉባኤን  በንግግር  የከፈቱት የኢፌድሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በዚህ የጥራትና የምርምር ጉባኤ የሚነሱ ውጤቶች በቀጣይ በጤናው ዘርፍ ለሚደረጉ ለውጦች አጋዥ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

በተለይም ደግሞ አመታዊ የጤና ሳይንስ ጉባኤ በአራት ቀን ቆይታው የመረጃ አብዩት፤ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፤ የስነ ምግባር፤ የድንገተኛ አደጋዎች ላብራቶሪና ባህላዊ ህክምና ላይ ትኩረት ተሰጥቶበት የጥናታዊ ስራዎች ይቀርባሉ፡፡

በዚህ ጉባዔ ላይ ከ500 በላይ ተመራማሪዎች፥ ተማሪዎች እና ባለድርሻ አካላት የተገኙበት ሲሆን ከ200 በላይ ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ገልጸዋል: :

በተያያዘም

በተጨማርም ከሰኞ ሚያዚያ 28 /2011 ዓ.ም  ጀምሮ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሲጋራ የማይጨስበት ተቋም መሆኑን አውጇል::

ጉባኤውን አስመልክቶ የተዘጋጀ ኢግዝቢሽን በጉባኤተኞቹ የተጎበኘ ሲሆን የኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ድኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ና በኢትዮጵያ የ CDC country Director ዶ/ር ክርስቲን ሮዝ በጉባኤው ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል: :

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami