አልበሽር ለሰልፍ በወጡ ተቃዋሚዎች ግድያ ተከሰሱ፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበዉ ክሱ የእርሳቸውን አስተዳደር በመቃወም አደባባይ በመውጣት ህይዎታቸው ባለፉ ዜጎች ምክንያት ነዉ፡፡
ኦማር ሃሰን አልበሽር ሱዳንን ለ30 አመታት ያክል የመሩ ሲሆን
ባለፈው ሚያዚያ ወር ም በህዝባዊ ተቃውሞ ከስልጣን መዉረዳቸዉ ይታወሳል፡፡
አሁን ላይ በማረሚያ ቤት የሚገኙት አልበሽር ከህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ በሚል ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራም ይገኛል፡፡
አልበሽር ቤተሰቦቻቸው በህገ ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀም ወንጀል የተመሰረተባቸውን ክስ እንዲከራከሩላቸው አራት ጠበቆችን ቀጥረውላቸዉ ነበር ፡፡