የአልጀሪያ ተማሪዎች ጥያቂያችን ሳይመለስ ምርጫ ብሎ ነገር የለም እያሉ ነው፡፡
ተማሪዎቹ ረመዳን ከገባ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከተሞች ለሁለተኛ ጊዜ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አልጀሪያውያን በጊዜያዊ ፕሬዝዳንቱ አብደልከድር ቤንሳላህ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አላቸው፡፡
በዚህም የተነሳ የህዝቡ ፍላጎት ሳይሟላ በመጭው ሰኔ እንዲካሄድ ቀን የተያዘለት ምርጫ ይሳካል ብሎ ማሰብ እንደማይቻል የሚያሳስብ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል፡፡
ሰልፈኞቹ ከያዟቸው መፈክሮች መካከል ተማሪዎች የነፃነት ወታደሮች ናቸው እናም በቀላሉ አይሸነፉም የሚለው ይገኝበታል፡፡
የፕሬዝዳንት አብደልአዚዝ ቡተፍሊካን መንግስት በአመፅ ከዙፋኑ ያወረዱት ተቃዋሚዎቹ የፕሬዝዳንቱ የቅርብ ሰዎች በስልጣን ላይ መቀመጣቸው የስርዓት ሳይሆን የሰው ለውጥ ነው በማለት ቁጣቸው በርትቷል፡፡