PoliticsWorld News

ትራምፕ ስደተኞችን ችሎታ እና እድሜ ላይ ባተኮሩ መስፈርቶች እንቀበላን አሉ፡፡

ትራምፕ ስደተኞችን ችሎታ እና እድሜ ላይ ባተኮሩ መስፈርቶች እንቀበላን አሉ፡፡

በስደተኞች ጉዳይ በብጥቅየሚተቹት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ  ሀገራቸው ስደተኞችን  የምትቀበልበት አዲስ ፖሊሲ ለማውጣት አቅደዋል፡፡

በዚህም መሰረት ወደ አሜሪካ ለመግባት አንዱ መለኪያ ወጣትነት  እንደሆነ ከዋይት ሀውስ የወጣው መረጃ ያሳያል፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ወጣት መሆን በራሱ ግን ብቸኛ መስፈርት አይደለም፡፡ በተጨማሪም በትምህርታቸው የገፉ እና እንግሊዘኛን አቀላጥፈው የሚናገሩ ሰራተኞች አሜሪካ ገብተው እንዲሰሩ ይበረታታሉ በአዲሱ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ፡፡

ትራምፕ ይህን ትልቅ ለውጥ የምናደርገው ወደ ሀገራችን ገብተው በእውቀት እና  በክሎታቸው ውጤታማ ስራ የሚሰሩ ሰዎችን ቁጥር ለማብዛት  ነው ብለዋል፡፡

በፕሬዝዳንቱ የቀረበው አዲሱ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ተግባራዊ ከሆነ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች ከትምህርት እና ከእንግለዝኛ ችሎታ በተጨማሪ የሲቪክስ ፈተና ወስደው ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አዲሱ የትራምፕ እቅድ የሪፓብሊካን ፓርቲ ተወካይ ከሆኑት የምክር ቤት አባላት  ተቃውሞ ቀርቦበታል፡፡

ለተቃውሟቸው አንዱ ምክንያት አዲሱ የፖሊሲ እቅድ አሜሪካ የሚገኙ 11 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን አያካትትም የሚል ነው፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami