EthiopiaSportSports

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የተካሄዱ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መልካም ውጤት አስመዝግበዋል::

ቅዳሜ ዕለት በተካሄደ የሻንጋይ የዲያመንድ ሊግ ውድድር ፡-

ወንዶች የ5000 ሜትር ርቀት ኢትዮጵያውያኑ ተከታትለው በመግባት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

  1. ዮሚፍ ቀጀልቻ… በ13:04.16
  2. ሰለሞን ባረጋ… በ13:04.71
  3. ሃጎስ ገ/ህይወት… 13:04.83

በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ደግሞ  

  1. ራባቢ አራፊ… በ4፡01.15 (ሞሮኮ)
  2. ጉዳፍ ፀጋዬ… በ4:01.25
  3. ዊኒ ናንዮንዶ… በ4፡01.39 (ኡጋንዳ)
  4. ዳዊት ስዩም… በ4:01.40 … በመሆን ሲጨርሱ አክሱማዊት እምባዬ 6ኛ እና አልማዝ ሳሙኤል 8 ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡ 3000 ሜትር መሠናክል ሴቶች የተወዳደረችው ወይንእሸት አንሳ 11ኛ ደረጃ ላይ ጨርሳለች፡፡

ትናንት በተካሄዱ ሌሎች ውድድሮች፤ ላቲቪያ ላይ በተካሄደው የሪጋ ማራቶን በወንዶች አንዷለም በላይ ኬንያውያን አትሌቶችን በማስከተል በ2፡08.51 ሲያሸንፍ፤ ኢትዮጵያውያን የበላይ በሆኑበት የሴቶች ውድድር ደግሞ ብርቄ ደበሌ በ2፡26.18 ቀዳሚ ስትሆን፣ ወርቅነሽ አለሙ በ2፡27.30 ሁለተኛ እና ቁመሺ ሲቻሌ በ2፡29.44 ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሰዋል፡፡

በዴንማርክ መዲና የኮፐንሀገን ማራቶን በሴቶች እታለማሁ ዘለቀ በ2፡29.29 አንደኛ፤ ድንቅነሽ መካሽ በ2፡30.22 ሁለተኛ፣ አበሩ አያና በ2፡34.39 ሶስተኛ እንዲሁም ንግስት ሙሉነህ አራተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል፡፡ በወንዶች ገብሬ ሮባ ሶስተኛ ሆኗል፡፡

በኔዘርላንድስ የሌይደን ማራቶን ደግሞ በሁለቱም ፆታ ኢትጵያውያን አትሌቶች ድል ሲያደርጉ፤ አለማየሁ መኮነን እና ደገፋ ዮሃንስ እንዲሁም በሴቶች ዘነቡ ፋንታዬ እና ቤንቱ ሽፈራው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው አሸናፊ መሆን ችለዋል፡፡

በኦስትሪያ ሳልዝበርግ ጋዲሴ ጉዲሳ በ2፡46. 37 አሸንፋለች፡፡

ጣሊያን ላይ የሜዛ ዴል ናቪግሊዮ ማራቶን በሴቶች አዲሳለም በላይ፣ አስመራወርቅ በላይ ተከታትለው በመግባት ባለድል ሆነዋል፡፡

በህንድ ቤንጋሉሩ 10 ኪ.ሜ አንዱአምላክ በልሁ በ27፡56 ጊዜ ቀዳሚ ሲሆን ብርሃኑ ለገሰ በ28፡23 ሶስተኛ ወጥቷል፤ በሴቶች ደግሞ አኜስ ቲሮፕ ከኬንያ፤ ለተሰንበት ግደይ እና ሰንበሬ ተፈሪ ከኢትዮጵያ በ33፡55 ጊዜ በማይክሮ ሰከንዶች ተቀዳድመው 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ሲወጡ እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያኑ ነፃነት ጉደታ፣ ደራ ዲዳ እና ፀሃይ ገመቹ ከ4ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ተቆናጥጠዋል፡፡

 

ምንጭ፡ አፍሪካን አትሌቲክስ ዩናይትድ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami