EthiopiaPolitics

ፍርድ ቤቱ ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ከ98 ቤቶች ውጪ ያሉት እንዳይተላለፉ የወጣው እግድ እንዲነሳ አዘዘ

ፍርድ ቤቱ ከ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ከ98 ቤቶች ውጪ ያሉት እንዳይተላለፉ የወጣው እግድ እንዲነሳ አዘዘ

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጦር ሀይሎች ምድብ ችሎት 8ኛ የፍትሃብሄር ችሎት እጣ ወጥቶባቸው የነበሩ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ ተጥሎ የነበረው እግድ ከ98 ቤቶች ውጪ ያሉት ቤቶች ላይ እግዱ እንዲነሳ አዘዘ።

መጋቢት 26 ቀን 2011 ዓመተ መህረት 98 ፤100 በመቶ ክፍያ የፈፀሙ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች ከሳሾች እጣ የወጣባቸው ቤቶች እንዳይተላለፉ የጠየቁትን አቤቱታን ችሎቱ ሲመረምር ቆይቷል።

እጣ የወጣባቸው ከ18 ሺህ በላይ ቤቶች መሆናቸው የተመለከተው ፍርድ ቤቱ፥ በእነዚህ 98 ተከሳሾች ምክንያት ሌሎች ቤቶች ታግደው መቆየት የለባቸውም ሲል የሌሎችን ቤቶች እግድ አንስቷል።

ፍርድ ቤቱ 98 ቤቶች ማለትም 48 ባለ ሶሰት መኝታ፣ 43 ባለ ሁለት መኝታ እና ሰባት ባለ አንድ መኝታ ቤቶች ባሉበት ለማንም ሳይተላለፉ ታግደው እንዲቆዩ ፥ በቀሪዎቹ ቤቶች ላይ ግን እግዱ እንዲነሳ ሲል ትእዛዝ ሰጥቷል።

በተጨማሪም ችሎቱ የፍትሃብሄር ህግ 41 መሰረት በእነ ዘላለም መዝገብ በሚል በአሁኑ እጣ የወጣላቸው ከ50 በላይ እድለኞች በሶስተኛ ወገን በመዝገቡ ላይ ጣልቃ እንግባ ብለው የጠየቁትን ጥያቄ ተቀብሎ ፈቅዷል።

ሌሎች 100 በመቶ ቆጥበናል ብለው የቀረቡ 130 ሰዎች ጥያቄን ውድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ፥ በሌላ መዝገብ እንደ አዲስ ክስ መመስረት ትችላላቹ ብሏል።

በሌላ በኩል 98 ቤቶች ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ ትእዛዝ የወጣላቸው 98 ከሳሾች ክሳቸውን አሻሽለው እና ለተከሳሽ ኪሳራ ከፍለው እንዲቀርቡ ለግንቦት 28 ቀን 2011 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

የጋራ መኖሪያ ቤቱን ለማግኘት ተመዝግበው 100 በመቶ የከፈሉ 98 ዜጎች ክስ መመስረታቸውን ተከትሎ ነው ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ የፍርድ ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለባለ እድለኞች እንዳይተላለፉ አግዶ የነበረው።

ተመዝጋቢዎቹም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒቴርን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝን እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ነው የከሰሱት።

ፋና እንደዘገበዉ በመመሪያው መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕጣ አውጥቶ ለእድለኞች ማከፋፈል ሲገባው የከተማ አስተዳደሩ መመሪያን በመጣስ 100 በመቶ የቆጠቡ ተመዝጋቢዎች እያሉ ከ40 በመቶ ጀምሮ የቆጠቡትን በእጣው በማካተት ዕጣውን በማውጣት ከሕግና ከውል ውጪ ቤቶቹ እጣ እንዳወጣባቸው በክሳቸው ላይ ጠቅሰዋል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami