ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃቢታት ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች
ከየተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ የማሻሻያ ሂደት ውጤት የሆነውና በናይሮቢ የተጀመረው የ1ኛው የተባበሩት መንግስታት ድጅት የሃቢታት ጉባኤ ኢትዮጵያን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል አድርጎ መርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኪንያ ገልጿል።
ኢትዮጵያ የስራ አስፈፃሚውን ቦርድ ለአራት አመታት እ.ኤ.አ ከ2019 – 2022 ድረስ ታገለግላለች።
ኢትዮጵያ የአፍሪካን አቋም በመደገፍና በማራመድ በኩል ያላትን የፀና አቋም ለአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ እንደሆነ አገራችንን ለቦታው በማጨት መግለፃቸው አገራችን በአፍሪካውያን ዘንድ ያላት የላቀ ተቀባይነት መቀጠሉን ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ኢትዮጵያም ለዚህ ምስጋናዋን በስራ አስፈፃሚ ቦርዱ ላይ የአፍሪካን አቋም በማንፀባረቅ ገልፃለች።
በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ፣ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ፣ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን መሪ ስም፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አለን መልዕክቱን አስተላልፏል።