EthiopiaSocial

 የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ የሚከለክለው  ድንጋጌ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል

የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ የሚከለክለው  ድንጋጌ ከዛሬ ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል

የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112 አንቀጽ 74(4) የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያን በብሮድካስት (ቴሌቪዥን እና ሬድዮ) እና በቢልቦርድ አማካኝነት የሚከለክለው ድንጋጌ ዛሬ ግንቦት 21, 2011ዓ.ም ተፈፃሚ መሆን ይጀምራል፡፡

በዚሁ መሰረት ማንኛውም የአልኮል መጠጥ አምራች ድርጅት ፣ የማስታወቂያ አስነጋሪ እና የብሮድካስት ሚድያ ለህጉ ተገዢ በመሆን በየቦታው የተሰቀለ ቢልቦርድ መነሳት እንዲሁም የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ በማንኛውም ብሮድካስት ሚዲያ ማስተዋወቅ መቆም ይኖርበታል ተብሏል::ሕብረተሰቡም ለዚህ ህግ ተፈፃሚነት ከጎናችን በመሆን በየቦታው የተሰቀሉ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ ቢልቦርዶች ስትመለከቱ እና የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎችን ስትሰሙ በ8482 እና የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ፌስቡክ ገፅ ላይ ጥቆማ እንድትሰጡ እንጠይቃለን ሲል የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ገልፀዋል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami