የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በተቃዋሚዎች ላይ የሀይል እርምጃ መውሰዱ አዲስ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡
የፀጥታ ሀይሎች ለተቃውሞ ጎዳና ላይ የሰነበቱትን ሰዎች ለመበተን ባደረጉት ሙከራ ግጭት ተቀስቅሶ 9 ሰዎች መገደላቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡
ህዝባዊ አመፁን በበላይነት የሚመራው የሱዳን ባለ ሞያዎች ማህበር በመላ ሀገሪቱ ለ 48 ሰዓታት የሚቆይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል፡፡
የተቃዋሚዎቹ ቃል አቀባይ ሸሪፍ ሞሀመድ ኦስማን ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ሀይሎች በሲቪሎች ላይ ያልተመጣጠነ ሀይል መጠቀማቸውን አውግዘዋል፡፡
በሀገሪቱ ዋነኛ ተቃዋሚ የሚባለው ኡማ ፓርቲ በበኩሉ ወታደራዊ ምክር ቤቱ የጀመረው የሀይል እርምጃ በድርድሩ የቀረችውን የተስፋ ጭላንጭል ያጠፋታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡
በምክር ቤቱ እና በተቃዋሚዎች መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው ድርድር በፍጥነት እንዲጀመር ፓርቲው ጥሪ አቅርቧ፡፡
መንገ ሻዓለሙ