AfricaSocial

ታንዛኒያኒያውያን በርካታ ህፃናትን እንዲወልዱ ከመሪያቸው ጥሪ ቀረበላቸው፡፡

ታንዛኒያኒያውያን በርካታ ህፃናትን እንዲወልዱ ከመሪያቸው ጥሪ ቀረበላቸው፡፡

በቅፅል ስማቸው ቡል ዶዘር በመባል የሚታወቁት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የሀገራቸው ሴቶች ብዙ ልጆችን እንዲወልዱ ጠይቀዋል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ማጉፉሊ ይህን ጥሪ ያቀረቡበትን ምክንያት ሲያብራሩ ብዙ የሰው ሀይል ያላት ሀገራ ጠንካራ ኢኮኖሚ የመገንባት አቅሟም በዚያው ልክ ከፍ ይላል የሚል ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከዓለማችን ቻይን እና ህንድን ከአፍሪካ አህጉር ደግሞ ናይጀሪያን ለአብነት በመጥቀስ በአግባቡ ከመሩት የሰው ሀብት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ አብራርቷል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ሀሳባቸው በተቃዋሚዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ነው የተባለው፡፡ የተቃዋሚዎቹ መከራከሪያ ደግሞ የ55 ሚሊዮነን ህዝብ ባለቤት የሆነቸው ታንዛኒያ በዓለማችን ፈጣን የህዝብ እድገት ያላት በመሆኑ እንዲያውም መመጠን ያስፈልጋል የሚል ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ የታንዛኒያ የህዝብ እድገት መጠን በየዓመቱ በአማካይ ከ6 እስከ 7 በመቶ ሲሆን በአንድ ቤተሰብ ከአምስት ያላነሱ ህፃናት ይገኛሉ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami