ሱዳን በ11 አባላት የሚመራውን አዲሱን ሉዓላዊ ምክር ቤት መሰረተች፡፡
የሱዳን ተቃዋሚዎች እና ጊዜያዊ ወታደራዊ ምክር ቤት ለወራት ከተደራደሩ በኋላ ለሶስት ዓመት ሀገሪቱን የሚመራውን ምክር ቤት በይፋ መስርተዋል፡፡
ምክር ቤቱን በበላይነት የሚመሩት አባላቱ አምስቱ ከጦር ሀይሉ አምስቱ ከተቃዋሚዎቹ የተውጣጡ ሲሆኑ አንደኛው ደግሞ ሁለቱ ተስማምተው በጋራ የመረጡት ነው ተብሏል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው አዲሱ ምክር ቤት ለሶስት ዓመታት ሀገሪቱን ከመራ በኋላ ሀገራዊ ምርጫ ተካሂዶ የሲቪል መንግስት ይአንዲቋቋም ነው ሁለቱ ወገኖች የተስማሙት፡፡
ምክር ቤቱ ከተመሰረተ ማግስት ጀምሮ የሚቀጥሉትን 21 ወራት ከወታደራዊ ምክር ቤቱ የተወከሉት ሌተናል ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሀን የሚመሩት ሲሆን ቀሪዎቹን 18 ወራት ደግሞ ተቃዋሚዎቹ ይመራሉ፡፡
ወታደራዊ ምክር ቤቱ እና ተቃዋሚዎቹ ተስማምተው በጋራ ለሶስት ዓመት የሚያስተዳደርሩት የሽግግር ካውንስል 300 የሚሆኑ ህግ አውጭ አባላት እንደሚኖሩትም ታውቋል፡፡
መንገሻ ዓለሙ