AfricaSocial

ናይጀሪያ ደቡብ አፍሪካን አስጠነቀቀች፡፡

ናይጀሪያ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቀቀች፡፡

አቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች፡፡

የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የናይጀሪያው የፕሬዝዳንት ማማዱ ቡሀሪ እና  የደቡብ አፍሪካው አቻቸው ሲሪል ራፋሞሳ በመጭው ጥቅምት ተገናኝተው በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

የናይጀሪያ መንግስት በዜጎቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተቀባይነት የሌለው እና ወደ አላስፈላጊ ውዝግብ የሚያስገባ ብሎታል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የዛምቢያ መንግስትም ለደቡብ አፍሪካ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እዲያስቆም ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከዚህም ባለፈ ከዛምቢያ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚገቡና የሚወጡ አሽከርካሪዎች ከመንግስት መመሪያ እስኪደርሳቸው ድረስ ጉዞ እንዲያቆሙ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

የደቡብ አፍሪካ መንግስት ሁኔታውን ለማስቆም በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም ነገሩ ቀላል እንዳልሆነለት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami