ደቡብ ሱዳን አሜሪካ እንድትታገሳት የተማፅኖ ጥያቄ አቀረበች፡፡
የደቡብ ሱዳን መንግስት ዋነኛ ደጋፊ የሆነችው ዋሽንግተን ደቡብ ሱዳናዊያን ተቀናቃኝ ሀይሎች የአንድነት መንገግስት ለመመስረት ዳተኝነት አሳይተዋል በሚል ቅሬታዋን መግለጿን ተከትሎ ነው ጁባ አቤቱታውን ያቀረበችው፡፡
ሁለቱ ወገኖች የጥምር መንግስት ለመመስረት ይዘውት የነበረውን ቀጠሮ ለተጨማሪ 100 ቀናት በማራዘማቸው ቅር የተሰኘችው አሜሪካ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያለኝን ግንኙነት ዳግም መፈተሸ አለብኝ የሚል አቋም ላይ ደርሳለች ነው የተባለው፡፡
የደበብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አለም አቀፍ ትብብር ቃል አቀባይ ማዌን ማኮል አሜሪካ የሰላም ሂደቱን መደገፏን እንዳታቆም ስንጠይቅ እኛም የአሁኑ ቀጠሯችን የመጨረሻው እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው የጥምር መንግስት ምሰረታው የተራዘመው የተቃዋሚ መሪው ሪክ ማቻር ገና ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች ስላሉን እነሱን ስንጨርስ ሁሉም ነገር ይደርሳል የሚል ሀሳብ በማቅረባቸው ነው፡፡
መንገሻ ዓለሙ