አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ላይ ይበልጥ መስራት እንደሚያስፈልግ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተናገሩ፡፡ ይህንን ያሉት ከምክርቤቱ 14ተኛ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የጤና ሚኒስትርና የህብረተሰቡ ጤና እንስቲትዮት በሀገሪቱ ቫይረሱን በተመለከተ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች በአብራሩበት ወቅት ነዉ ፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በየብስ በአየርም 520 ሺ የሚሆኑ መንገደኞች ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን 958ቱ ላይ ክትትል እየተደረገባቸዉ እንደሆነ የህብረተሰብ ጤና እንስቲትዮቱ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ አስረድተዋል፡፡
ኮሮና በኣለም የመኖርና ያለመኖር ስጋትን በከፍተኛ ደረጃ እንደፈጠረ የተናገሩት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በከፍተኛ ደረጃ የማህበራዊ መስተጋብርን የሚያበላሽ መሆንኑን ገልፃዉ፤ በሽታዉን ለመከላከል በርካታ ስራዎች ቢሰሩም በቂ የሆነ አቅም ግን እንደሚያስፈልግ ነዉ የተናገሩት ፡፡
የህዝብ ተወካዮች አባላቱም በጉዳዮ ላይ እስካሁን የተሰሩ ስራዎች መልካም የሚባሉ መሆናቸዉን ገልፀዉ ፡ቅድመ መከላከል ላይ ግን አሁንም በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜም 114 የሚሆኑ ሀገራት ተጠቂዎች አንደሆኑ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡