EthiopiaHealth

ኮሮናቫይረስ ያለበት ጃፓናዊ በኢትዮጵያ መገኘቱ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ።

ሚኒስትሯ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት አንድ ከሶስት ቀን በፊት ከቡርኪናፋሶ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ጃፓናዊ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል።
ከዚህ ቀደም ብሎ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ታከለ ኡማ በትዊተር ገፃቸው ላይ አንድ ጃፓናዊ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል ሲሉ አስታውቀው ነበር።
ከንቲባው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መውሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄ በመልዕክታቸው ላይ ጨምረው አስፍረዋል።
ሚኒስትሯ እንዳሉት ጃፓናዊ ትኩሳትና ማሳል የመሳሰሉ የቫይረሱ ምልክቶችን የሚያሲይ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛል ብለዋል።
የጤንነቱ ሁኔታም መጥፎ የሚባል አንዳልሆነ ገልፀዋል።
ከንቲባው “አንድ ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች አንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች መልዕክታቸውን አስፍረዋል።
(FBC)

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami