COVID-19EthiopiaFeaturedHealthNews

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 74 ደረሰ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2012 በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 74 ደረሰ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 247 ግለሰቦች መካከል፤ ሶስቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር ገለጿል።ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ከተረጋገጠባቸው ግለሰቦች መካከል ተጨማሪ አራት ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ በላኩት መግለጫ እንደገለጹት፤ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሶስቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም።ሶስቱም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ መሆናቸው ነው የተገለጸው።

ከግለሰቦቹ መካከል ሁለቱ ወንዶች ሲሆኑ፤ሁለቱም ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳላቸው ገና አልተረጋገጠም።አንዷ የ23 ዓመት እድሜ ያላትና ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳላት መረጋገጡን መግለጫው አመላክቷል።ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 74 ደርሷል።በሌላ ዜና ቫይረሱ እንዳለባቸው ከተረገጠባቸው ግለሰቦች መካካል ተጨማሪ አራት ግለሰቦች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን፤ይህን ተከትሎም በአጠቃለይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 14 ከፍ ብሏል።በኢትዮጵያ እስካሁን ለ4 ሺህ 110 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami