AfricaFinanceNewsPolitics

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለአራት ቀናት በተካሄደ የእርስ በርስ ግጭት 43 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለአራት ቀናት በተካሄደ የእርስ በርስ ግጭት 43 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ፡፡አጃንስ ፍራንስ ፕረስ የወታደር ባለስልጣናትን ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ ሁለት ግዛቶች በተፈጠረ ግጭት 43 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በግጭቱ አርብ እለት ጥቃት አድራሾች ስለትና የጦር መሳሪያ በመጠቀም 21 ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነው አጃንስ ፍራንስ ፕረስ የዘገበው፡፡

በድንበር አቅራቢያ በምትገኝ ዲጁጉ ከእሁድ እለት አንስቶ ግጭት እንደነበር የተነገረ ሲሆን ሁለት ወታደሮችንና ሁለት ንጹኃን ተገድለዋል፡፡እሁድ እለት በሰሜን ኪቩ ግዛት በተቀሰቀሰ ግጭት ስድስት ንጹሃን የተገደሉ ሲሆን አምስት ወንዶችንና አንድ ሴት መሆናቸውም ተነግሯል፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምርመራ ቡድን ባወጣው መረጃ ኢቱሪ በምትባል አከባቢ ከፈረንጆቹ 2017 ማለቂያ አንስቶ በነበረ ግጭት ከ7 መቶ በላይ ንጹሃን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፡፡

 

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami