AfricaCOVID-19FeaturedHealthNews

ደቡብ አፍሪካ የቲቢ ክትባትን ኮቪድ 19ን ለመከላከል  ይውል ዘንድ ሙከራ መጀመሯን ይፋ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2012 ደቡብ አፍሪካ የቲቢ ክትባትን ኮቪድ 19ን ለመከላከል  ይውል ዘንድ ሙከራ መጀመሯን ይፋ አደረገች፡፡የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ 19 ክትባት ለማግኘት የምርመርና የሙከራ ስራ በመስራት መጠመዳቸው ነው የተነገረው፡፡አምስት መቶ የጤና ባለሙያዎች ለዚሁ ስራ የተመደቡ ሲሆን የክሊኒካል የምርመር ተቋማት ደግሞ የምርምር ስራዉን በገንዘብ ይደግፋሉ ተብሏል፡፡በኬፕታውን  ክትባቱ የሚሞከርባቸው 3ሺ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ተዘጋጅተው ለአንድ ዓመት ያህል  ክትትል ይደረግላቸዋል  ነው የተባለው፡፡ለ250 በጎ ፈቃደኞች ክትባቱ የተሰጣቸው ሲሆን ለ250 ሰዎች ደግሞ መድሃኒትነት የሌለው ክትባት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም የተደረገው የክትባቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥና ምርምር ለማድረግ ይረዳ ዘንድ መሆኑ ተነግሯል፡፡ኮቪድ 19 የመተንፈሻ አከላን የሚያጠቃ በሽታ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ክትባትና መድሃኒት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት በዓለም ዙሪያ የሚካሔዱ የክትባትና የመድሃኒት ሙከራዎችን በበላይነት የሚቆጣጠር ሲሆን ለኮቪድ 19 ይውላሉ ተብለው በሚታሰቡ የወባና የቲቢ መድሃኒትና ክትባቶች ላይ እጥረት እንዳይፈጠር  ያለውን ስጋት መግለጹን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami