አዲስ አበባ፣ግንቦት6፣2012 ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመቆጣጠር በኩል ውጤታማ ስራ ተከናውኗል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለፁ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፉት ጥቂት ወራት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመቆጣጠር በኩል ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት ባለፉት ጥቂት ወራት ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ በመያዝ አኩሪ ሥራ ተሠርቷል።
በትናንትናው እለት ከክልል አመራሮች ጋር በነበራቸው ውይይት፣ በሕገ ወጥ መንገድ የጦር መሣሪያ ማስገባት እና ማዘዋወርን ለመግታት ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ መምከራቸውንም ገልጸዋል።ከእያንዳንዱ ምንጭ ወደ ሀገር የሚገባውን የመሣሪያ ዝውውር በአግባቡ ለመከታተል እና ሕገ ወጥ መሣሪያ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሁላችንንም ሥምሪት ይጠይቃል ብለዋል።