COVID-19EthiopiaFeaturedHealthNews

ኮቪድ 19ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል አሉ ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 ኮቪድ 19ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል አሉ ጠ/ሚ ዐቢይ::

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ፈጠራን በተመለከተ ባስተላለፉት መልእክት፥ ብዙዎቹ የፈጠራ ውጤቶች የፈተና ልጆች ናቸው ይባላል ብለዋል።

የሰው ልጆች ከዛሬው ሥልጣኔያቸው ላይ የደረሱት በየዘመናቱ የተደቀኑባቸውን እንቅፋቶች ለማለፍ እውቀትና ክሎታቸውን በስፋት በመጠቀማቸው የተነሣ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል።
አንዳንድ ሊቃውንት ሲናገሩ “እኛ ሰዎችን ለዛሬው ክብር ያበቃን አዕምሮ ያለው ፍጡር በመሆናችን እና አዕምሯችንን እንድንጠቀም በሚያስገድዱ ሁኔታዎች ውስጥ በማለፋችን ነው” ይላሉ ያሉት ዶ/ር ዐቢይ እነዚህ ሁለቱ ባይኖሩ፣ ሁላችንም ከዛፍ ወደ ዛፍ ተንጠላጣይ ሆነን እንቀር እንደነበርም ይናገራሉ ሲሉም ገልፀዋል።

ኮቪድ 19`ን ተከላክለን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ባለን ሀብት ላይ እውቀትና ፈጠራን አቀናጅተን መጠቀም ይኖርብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በመጭው ክረምት ያቀድነውን የ5 ቢልዮን ችግኝ ተከላ ወገባችንን አሥረን ማሳካትም ይኖርብናል ብለዋል። በተጨማሪም ዜጎች በቤት ሲቀመጡ ሊያከናውኗቸው የሚገቡ የሞያና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ከማትጋት በዘለለ የሀገር ፍቅርና የሕዝቦች አንድነትን ማጠናከር እንዳለብን ገልጸዋል፡፡

በዚህ መልኩ ለወረርሽኙ ስርጭት እድል ሳንፈጥር ለሀገር ግንባታ ከተጋን ያለ ጥርጥር ኮሮናም በቀላሉ ይሸነፋል፤ ሀገራችንም በብልጽግና ጎዳና ትራመዳለች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸዉ፡፡

Tags
Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami